በስኬት አጠናቀናል


አልታ ካውስሊንግ ለ 6 ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን የመሠረታዊ ካውንስሊንግ ክህሎት ሥልጠና በስኬት አጠናቋል፡፡ ጋዜጠኛ፣ ሳይኮሎጂሰት፣ ሶሻል ወርከር እና ማህበራዊ ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡ በዚህ ሥልጠና የሁልጊዜ ተባባሪያችንና ወዳጃችን የአዲስ አበባው ዩኒቨርሲቲ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ክፍል መምህር ዶ/ር አለማየሁ ተ/ማሪያም በመገኘት ከሙያው ጋር የተያያዘ ሥልጠናና እና ተሞክሮውን አካፍሎናል፡፡ የአልታ ካውንስሊንግ ሠራተኞች እውቀታቸውንና ተሞክሯቸውን በሰፊው ሠጥተዋል፡፡ ንቁ ተሳታፊ ሰልጣኞች መሆናቸው ቀናቶቹ አጭር ሆነውብናል፡፡
ከሠልጣኞቻችን አንደበት በጥቂቱ!
“ይህንን ሥልጠና የፈለኩበት ምክንያት በካውንስሊንግ ሥራ ላይ መሰማራት ስለምፈልግ ነው፡፡ — ተግባርና ንድፈ ሃሳብን ያካተተ አጭር ሥልጠና ባገኝ ብዬ ሳስብ ነበር፡፡ እናም ይህን የአልታ ካውንስሊንግ ሥልጠና አገኘሁ፡፡ በዚህ ስልጠና መሰረታዊ የካውንስሊንግ ሙያ ንድፈ ሃሳብ፣ እውቀትና ክህሎት በማግኘቴ ደስ ብሎኛል፡፡ በዚህ ስልጠና በዋናነት ራሴን ተመልክቼበታለሁ፡፡ —ለቀሪ ህይወት ዘመኔ ስንቅ የሚሆን እውቀት አግኝቼአለሁ፡፡ — በሌላ በኩል ከሙያው ጋር በተያያዘ በግሌ የነበሩኝን የተዛቡ፣ ልክ ያልሆኑ አስተሳሰቦችንም ለማጥራት ጠቅሞኛል፡፡
ሥልጠናው የተሰጠበት መንገድ (ፋሲሊቴሽን ስኪል) ጥሩ ነበር፡፡ የአልታ ካውንስሊንግ ባለቤት አቶ ወንድወሰንን በልዩ ሁኔታ ማማስገን እፈልጋለሁ፤ ካለው ሰፊ የሆነ ልምድና የህይወት ተሞክሮ ጋር መሰረታዊውን ሳይንስ አቀናጅቶ የሰጠበት መንገድ አስደስቶኛል፡፡”
“Wow! እጅግ በጣም ጥሩ ከማለት በላይ የሆነ ሥልጠና! ሳይኮሎጂ ስንማር ካገኘሁት ጥቅም በላይ በዚህ ስድስት ቀን ያገኙት ጥቅም ማስተርሴን የመያዝ ያህል ነው የቆጠርኩት፡፡ —እባካችሁ ሪሰርች ላይም ሆነ ማንኛውም አገልግሎት ላይ በፈቃደኝነት የሚሰራ ሰው ስትፈልጉ እኔ አለሁ፤ ሁላችሁንም አመሰግናለሁ”

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *